ላኮመንዛ ገበያ የሻጭ ድርጅቶች የምዝገባ መመሪያ

እባክዎ በቀላል መንገድ ድርጅትዎን ለመመዝገብ መጀመሪያ የሚያስፈልጉ ሰነዶችን እና መረጃዎችን ከታች ያንብቡ።

የሻጭ ምዝገባ መረጃ

የሚያስፈልጉ ሰነዶች

  • የድርጅት ባለቤት መታወቂያ (Digital ID)
  • የንግድ ሥራ ምዝገባ ማስረጃ (የንግድ ፍቃድ)

ለምን ሰነዶችን እንደምንጠይቅ ማወቅ ከፈለጉ ከታች ይመልከቱ

የምዝገባ ሂደት

  1. የድርጅት እና የባለቤት መረጃን መሙላት
  2. የንግድ ማረጋገጫ ሰነዶችን ማስገባት
  3. የደንበኝነት ጥቅል መምረጥ
  4. የተቀመጡ የክፍያ እማራጮችን መምረጥ
  5. በመረጡት የክፍያ አማራጭ ክፍያ ከፍለው ማረጋገጫ ደረሰኝ (እስክሪንሻት) ማስገባት
  6. ትክክለኛ የሚጠቀሙበትን ኢሜይል ማስገባት (ፓስወርድ ከረሱ ደግመው መቀየር ይረዳዎታል)
  7. ጠንካራ እና ሌሎች ሊገምቱት የማይችሉትን የይለፍ ቃል (ፓስወርድ) ማስገባት

ምዘገባ ፎርሙን ለመሙላት ጊዜ የለዎትም ? ወይስ አልተረዱትም ? ምንም ሳይጨናነቁ ድርጅትዎን እኛ እንመዘግብልዎታለን

ይደውሉ

የምዝገባ ማጠቃለያ

  1. ያስገቡት የብር መጠን ከተጠቀሰው በላይም በታችም መሆን የለበትም
  2. የከፍያ ማረጋገጫ ደረሰኝ በጥራት የሚታይ መሆን አለበት
  3. የ ድርጅት ሰነዶች ትክክለኛ መሆን እና በጥራት የሚታዩ መሆን አለባቸው ( ከማጽደቃችን በፊት ስለምናረጋግጥ )
  4. ከላይ የተጠቀሱትን መረጃዎች በትክክል ካስገቡ ምዝገባዎ ከ 2 እስከ 3 ሰአታታት ውስጥ ጸድቆ ማረጋገጫ በኢሜይል የደርስዎታል ሲመዘገቡ ያስገቡትን ኢሜይል እና ፓስወርድ በማስገባት ሱቅዎን ማስተዳደር ይጀምራሉ።

ሁሉም መረጃ ግልጽ ከሆነልዎት

ወደ ምዝገባ ይሂዱ

ግልጽ ካልሆነልዎ ከታች ተደጋጋሚ ጥያቄዎችን ይመልከቱ ወይም በቀላሉ

ያናግሩን

የ ደንበኝነት ጥቅሎችን ከታች መመልከት ይችላሉ።

የደንበኝነት ጥቅል ዋጋዎች

ሰነዶችን የምንጠይቀው ለምንድን ነው?

የምንጠይቃቸው ሰነዶች የሚያገለግሉት ለሚከተሉትን ዓላማዎች ነው።

  • የንግድ ድርጅቱን ህጋዊነት ለማረጋገጥ
  • የ ገዥዎችን ግብይት ታማኝነት እናዲኖረው ለማድረግ
  • ላኮመንዛ ገበያን ለ ገዥዎችም ለሻጮችም ምቹ እና ደህንነቱ የተጠበቀ የገበያ ቦታ እንዲሆን ለማድረግ

ተጨማሪ ምክንያቶች፡-

  • ሀጋዊ የገንዘብ ዝውውር እናዲኖር
  • የገንዘብ ምንዛሪ ሕጋዊነት ለማረጋገጥ
  • የእርስዎን የንግድ ብቃት ለማረጋገጥ
  • የስርዓታችን ደህንነት ለማረጋገጥ

ተጨማሪ ያንብቡ

ተደጋጋሚ ጥያቄዎች (FAQ)

የምዝገባ ሂደት በጣም ቀላል በሆነ መንገድ በ አንድ ፎርም የተካተተ ስለሆነ ቢበዛ በ 10 ደቂቃ ውስጥ የሚያልቅ ሲሆን ሁሉም ሰነዶች ከተላኩ እና ክፍያው ከተከናወነ በኋላ ከ 2 እስከ 3 ሰአት ባለው ውስጥ ተረጋግጦ የማረጋገጫ ደረሰኝ እና መመሪያ በ ተመዘገቡበት ኢሜይል ይላካል ።

ትክክለኛ ያልሆኑ ሰነዶችን እንዲሁም ክፍያ ሳይከፍሉ ከተመዘገቡ ወዲያወኑ ምዝገባው ይሰረዛል።

ሲመዘገቡ ተክክለኛ የሚጠቅሙበትን ኢሜይል ከሆነ ያስገቡት ፓስወርድ ረስቻለው የሚለውን በመጫን በ ኢሜይልዎ ኮድ ይደርስዎታል እሱን በማስገባት አዲስ ፓስወርድ መቀየር ይችላሉ።

የምዝገባ ማረጋገጫ ካገኙ በኋላ፣ የእርስዎን የምርት/አገልግሎት በመመዝገብ ለሽያጭ ያቅርባሉ የሱቅዎን እንቅስቃሴ መከታተል ይችላሉ።

የእርስዎ የግል መረጃ የድርጅትዎ እንዲህም የግብይት መረጃዎች በSSL ኢንክሪፕሽን እና የደህንነት ፕሮቶኮሎች የተጠበቀ ነው። የእርስዎን መረጃ ከሶስተኛ ወገን ጋር አናጋራም ለበለጠ መረጃ ውሎች እና ደንቦችን እዚህ ይመልከቱ።

በላኮመንዛ ገበያ ከ ገዥዎች ሻጮች ጋር ልሚፈጠሩ አለመግባባቶች ጣልቃ ገብተን ችግሮችን ለመፍታት እንሞክራለን በሁለቱም ወገን ችግሮችን መፍታት ካልተቻለ እንዲሁም ተጎጂ ነኝ ብሎ ወደ ሀግ ለሚሄድ አካል ሙሉ በሙሉ እንተባበራለን እንዲሁም አስፈላጊ የግልም ይሁን የድርጅት መረጃ ስንጠየቅ ለህግ አካል እናቀርባለን።

አዎ፣ እያንዳንዱ ሻጭ ድርጅት ምርቶችን ለሽያጭ ሲለቅ ለ ገዥዎች በቀላሉ የሚነበብ የምርት ስም ትከክለኘ ምርቱን የሚገልጽ ምስል ትክክለኛ ዋጋ እንዲሁም የምርት ዝረዝሮችን በተገቢ መንገድ መዘርዘር ይኖርብዎታል ለምሳሌ ትክክለኛ ሳይዝ ፤ ከለር ፤ ምርት አገልግሎት የሚያልቅበት ጊዜ ካለው ፤ እንዲሁም እንደ መርቱ አይነት አስፈላጊ ዝርዝሮችን እና መረጃዎችን መመዝገብ ግዴታዎች ናችው እነዚህን ተከትሎ ለሚመጡ ቅሬታዎች ሙሉ ሀላፊነቱን ሻጮች ይወስዳሉ። ለበለጠ መረጃ እዚህ ይመልከቱ

ለተጨማሪ እርዳታ የደንበኞች አገልግሎት ቡድናችንን በስልክ ቁጥር +251-XXX-XXXXXX ወይም በኢሜይል support@example.com ማግኘት ይችላሉ። የስራ ሰአት፡ ከሰኞ-አርብ ጠዋት 2፡00 እስከ ምሽት 4፡00 ድረስ ነው።

የምዝገባ ክፍያ አንዴ ከተከፈለ የማይመለስ ነው። ነገር ግን፣ ከተጠቀሰው የክፍያ መጠን በላይ ካስገቡ ክፍያውን ተጨማሪ ያስገቡትን መጠን እንመልሳለን እንዲሁም ከተጠቀሰው የክፍያ መጠን በታች ካስገቡ ቀሪውን እንዲጨምሩ እናደርጋለን።

አዎ፣ አንድ ሻጭ በተለያዩ ስሞች እና መረጃዎች ብዙ ሱቆችን መመዝገብ ይችላሉ። ነገር ግን እያንዳንዱ ሱቅ የራሱ የሆነ የምዝገባ ክፍያ እና ሰነዶች ያስፈልገዋል።